አባባሎች እና ጥቅሶች

313

ቋንቋ

app
ሌት ተቀን ሌላ እንድትሆን በሚገፋፋህ ዓለም ውስጥ እራስን ሆኖ መገኘት ትልቅ ውጤታማነት ነው
መሪነት ጥበብ እንጂ ጉልበት አይፈልግም
እንዴት እንደሚነበብ ካወቅን ሰው ሁሉ መጽሐፍ ነው
ሁሌም ጥግ ቆመህ ለምን ይዘንባል ብለህ አታማር ፤ ዣን ጥላ ይዘህ በዝናብ መጓዝን ልመድ
መብረር ካልቻልክ ሩጥ ፤ መሮጥ ካቃተህ ተራመድ ፤ መራመድ ቢሳንህ ተንፏቀቅ እንጂ ባለህበት አትቀመጥ
ሰውን ስትቀርብ ልክ ይኑርህ ፤ በጣም ጣፋጭ አትሁን ተልሰህ ታልቃለህ በጣም መራር አትሁን ትጠላለህ
በፍጥነት መሄድ ከፈለክ ብቻህን ሂድ፤ እሩቅ መሄድ ከፈለክ አብረህ ሂድ
ቤት ውስጥ ሸረሪት ድር ቢያደራ ድሩን ማፅዳት ዘለቄታዊ መፍትሄ ሊሆን አይችልም ፤ ሸረሪቷን ማስወገድ እንጂ
አንድን ሰው ስትተዋወቀው በልብሱ ልትመዝነው ትችላለህ፤ ስትለየው ግን በአስተሳሰቡ ትመዝነዋለህ
ዛሬ በውሸታሞች የተዋሸኸው ውሸት ስሜትህን ከመጉዳትም አልፎ ነገ እውነተኛ ሰዎችን እንዳታምን ያደርግሃል
የሚወዱህ ከተናደዱብህ ስህተት ሰርተሀል ማለት ነው ፤ የሚጠሉህ ከተናደዱብህ ግን ትክክል ሰርተሀል ማለት ነው
እርቀህ ከመሄድህ በፊት መንገድህ ልክ መሆኑን እርግጠኛ ሁን
ወደ ስኬት መንደር የሚያደርሰውን ነባሩን ጎዳና ካጣኸው የራስህን አዲስ መንገድ ፍጠር
ብልሆች እውቀት ይከተላሉ ፤ ሞኞች ሰውን ይከተላሉ
ኮርጀህ ከሚሳካልህ በራስህ ጥረት ሰርተህ ብትወድቅ ይሻላል
ሰውን ስትጎዳ ብድር እንደሰጠህ ቁጠረው ፤ ቆየት ብሎ ከነወለዱ ይመለስልሀል
ባለማስተዋላችን እንጂ ሳያስተምረን የሚያልፍ አንድም ቀን የለም
ተቀባይነት ለማግኘት ብለህ በጭራሽ ማንነትህን አትቀይር
"በሌቦች ብልጽግና እንዳልቀና፣ በክፉ ሰዎች ተድላም እንዳልጎመጅ አግዘኝ" ብሎ ፈጣሪን መማፀን ብልህነትም ልባምነትም ነው
የሴት ልጅ ታማኝነት የሚለካው አጋሯ ምንም በሌለው ጊዜ ሲሆን ፤ የወንድ ልጅ ደግሞ ሁሉም ነገር ባለው ሰዓት ነው
ሁሉ ነገር በጊዜው ይሆናል። አበባ ጊዜዋ ሳይደርስ አትፈካም፤ ፀሀይም ከሰዓቷ ቀድማ አትወጣም
ሁሉን ነገር መጠራጠር ከንቱ ቢሆንም ሁሉን ነገር አምኖ መቀበል ግን የበለጠ ከንቱ ነው
ጫማዎች እና ሰዎች ህመም እንዲሰማህ ካደረጉ ልክህ አይደሉምና ተዋቸው
ቀላሉ የሰውን ችግር አይቶ መፍረድ ነው፤ ከባዱ የራስን ችግር አውቆ መቀበል ነው
በ 1 ዓመት ውስጥ 10 ጓደኛ መያዝ ቀላል ነው፤ ለ 10 ዓመት ከ 1 ጓደኛ ጋር መዝለቅ ግን ድንቅ ነው
መስራት ባለብህ ሰዓት ካልሰራህ መሳቅ ባለብህ ሰዓት ታለቅሳለህ
ጨለማ ውስጥ ብርሀን መሆን ካቃተህ ብርሀን ውስጥ ጨለማ አትሁን
ግዴታ ሲሆን ብቻ አቅምህን አሳያቸው
አላማህ ከሌሎች መሻል ሳይሆን ከትናንትህ መሻል ይሁን
መልካም ሰዎች ልክ እንደ ጨረቃ ናቸው ዙሪያህ ሲጨልም ብርሃን ይሆኑልሃል
ፈጥነህ ሰውን አትመን “ጨው” እራሱ መጀመሪያ ስታየው “ስኳር” ይመስላል
ልታስደስተው ያልቻልከውን ልብ ሳታቆስለው ተወው
የምትወደውን እስክትሰራ የምትሰራውን ውደደው
አንድ ጥሩ ቃል የአንድን ሰው ቀን ታበራለች
ጊዜ የነበረህን እንድታደንቅ ከማረጉ በፊት ያለህን ማድነቅ ተማር
ብዙ ሰዎች ያውቁሃል ነገር ግን የሚረዱህ ጥቂቶች ናቸው
ብዙ ዝናብ ጥሎ ፀሀይ እንደሚወጣው ሁሉ ብዙ መከራ አልፎም ደስታ ይመጣል
አንዳንዴ በሰዎች ህይወት ውስጥ ጣልቃ አለመግባት በራሱ ሰዎችን መርዳት ነው
ልክ እንደ ብርጭቆ ሁን ፤ ከሰበሩህ ቁረጣቸው
አንዳንዴ ደግ ሰውን ለማወቅ ክፉ ሰው ይኑር
40